የተከበሩ የታኮማ ፓርክ እና የፓይኒ ብራንች የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ቤተሰቦች፣
ከዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እስከ አህመዱ አርቤር፤ ብሬናን ቴይለር፤ ፊናን በርሄ፤ ሮበርት ዋይት፤ እና ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ምክንያት እነዚህ ያለፉት ሶስት ወራታት ተፈታታኝ ነበሩ፡፡ የእነዚህ አሳዛኝ አሟሟት እና ከእነሱ በፊት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሌሎች መሞታቸው ብዙ ሰዎችን እና ቡድኖችን ወደ ተግባር እንዲነሳሱ ገፋፍተዋል፡፡ የእነሱ አሟሟት ሁኔታ እና የምናያቸው የሚሰቀጥጡት ድርጊቶች በአለም አቀፍ፣ በብሔራዊ፣ በስቴት እና በአከባቢያችን በዘር ፍትህ እና በእኩልነት ላይ ውይይት እንድናካሄድ እየቆሰቆሱ ነው፡፡
የዚህ ደማቅ ማህበረሰብ የወላጅ-አስተማሪ ማህበር (PTA) እንደመሆኔ፣ እኛ እነዚህን ክስተቶች አምነን መቀበል እና፣ ጥቁር፣ የአገሬው ተወላጅ እና / ወይም ቀለም ያላቸው ሰዎች (BIPOC) ፍላጎቶች ላይ በመመርኮዝ ወደ ተግባር መጓዝ እንፈልጋለን፡፡ በተጨማሪም የዘር ፍትህ እና እኩልነት ሌሎች ወደ ዳር ተገፍተው ያሉ ማህበረሰቦች እንደ ሂስፓኒክ/ላቲኖ በተሰናከለው የኢሚግሬሽን ሥርዓት እየተሰቃዩ ያሉትንም ማጠቃለል እንዳለበት እንገነዘባለን፡፡
በ PTA አባልነታችን፤ የበለጠ መሥራት እንደምንችል እናውቃለን እናም የበለጠ መሥራት እንደሚያስፈልገን እንገነዘባለን፡፡ እኛ ቃል እንገባለን የሚቀጥሉትን ለመተግበር፤
- በትምህርት ቤታችን ውስጥ ባህላዊ ምላሽ ሰጪ ማህበረሰብን ለማዳበር አጠቃላይ ውይይትን፣ ትብብርን፣ እርምጃን እና ትምህርትን በተመለከተ ግልጽ የልሆኑትን አድልዎችን የሚቀርፍ ዕድል መፍጠር፡፡
- በ PTA አመራር እና በአባልነት ውስጥ የተለያዩ ባህል እና ጾታ ያላቸውን አባላት ቁጥር ማሳደግ፡፡
- ከመምህራን ጋር ያለውን ትብብር ማሳደግ፣ በተለይም የተለያዩ ባህላዊ ልምዶች እና ባህሎች ላሏቸው ቤተሰቦች በጋራ ለመስራት እና በክፍል ውስጥም ሆነ ውጭ በትምህርቱ እና በመማር ላይ ፀረ-ዘረኝነት አቀራረብን ከፍ ለማድረግ።
- በ PTA ዝግጅቶች እና በ PTA ቁሳቁሶች ውስጥ የቋንቋ ትርጉም እና የትርጓሜ አገልግሎትን ማስፋት
ቀለም ያላቸው የትምህርት ቤታችን ቤተሰቦች ስለ ዘረኝነት መወያየት ለእነሱ አዲስ አይደለም፣ በማህበረሰባቸው እና በሚወዷቸው ሰዎች ላይ በቀጥታ እንዴት ጫና እንደፈጠረ ጨምሮ፡፡ በማህበረሰባችን እና በአለም ዙሪያ BIPOC ሰዎች ስላደረጉት አስደናቂ እና አስገራሚ አስተዋፅኦ ብዙዎች ከልጆቻቸው ጋር ውይይት እያደረጉ ነው፡፡ ልጆቻቸውን ማነጋገር ገና ላልጀመሩት እኛ በዘር፣ በልዩነት እና በተቋማዊ ዘረኝነት - እንዲሁም በተስፋ፣ በለውጥ እና በማህበራዊ ፍትህ ዙሪያ ከልጆችዎ ጋር አስቸጋሪ ውይይቶች እንዲያደርጉ እናበረታታለን፡፡ BIPOC ያልሆኑት አጋሮች እራሳቸውን የማስተማር እና ፀረ-ዘረኝነት እርምጃ መውሰድ መጀመር እንዲሁም ዘረኝነትን ማውገዝ እና በማህበረሰባችን እና በአገራችን ውስጥ የ BIPOC ቤተሰቦችን የመደገፍ ግዴታ አለባቸው፡፡ በትምህርት ቤታችን ማኅበረሰብ ውስጥ ዘላቂ የዘር ፍትህ እና እኩልነትን ለማሳካት በምናደርገው ጥረታችን ሁሉ እንዲሳተፉ በደስታ እንጋብዛለን እንዲሁም እናበረታታለን ፡፡
የ BIPOC ን ፍላጎት ለማርካት ብዙዎች በቤተሰቦች እና በማህበረሰቦች ውስጥ በአሁን ሰዓት በመሰራት ላይ እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ይህንን ለማድረግ ተጨማሪ መንገዶችን የሚፈልጉ ከሆነ ጊዜዎን፣ ችሎታዎን እና ገንዘብዎን በደል ለመቅረፍ እና የ BIPOC ን ኑሮ ለማሻሻል ለሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በልግስና ስለመስጠት ያስቡ፡፡ በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ መረጃዎች እና ተነሳሽነቶች ብዙ ናቸው፤ ጥቂቶቹ ቀጥሎ ተካትተዋል፤ ኤንኤኤሲፒ፤ ኢምፓክት ሲልቨር ስፕሪንግ፤ ካኣሳኣ፤ ሲልቨር ስፕሪንግ የፍትህ ቅንጅት፤ የዘር ፍትህ ዛሬውኑ!፤ ታኮማ ፓርክ ሞባላይዜሽን፤ እና ቺኢኢር፤ ተጨማሪ መረጃዎች እዚህ ያገኛሉ፡፡
በአንድነት ፣
ሜጋን ማክዶናልድ፣ የ PTA ፕሬዝዳንት በታኮማ ፓርክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ megholland@gmail.com
ሣራ ጎፔል፣ የ PTA ፕሬዚዳንት በፓይኒ ብራንች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ sgoupell@gmail.com
የአርትዑ መመሪያ እና ድጋፍ ለሰጡን፤ ርዕሰ መምህራኖቻችን፣ የ PTA NAACP ተወካዮቻችን፣ የ PTA እኩልነት ኮሚቴ አባላታ፣ የ PTA ሥራ አስፈፃሚ ቦርዱ፣ አስተርጓሚዎቻችን እና ግንዛቤያቸውን እና እውቀታቸውን ላካፈሉ ሌሎች የማህበረሰብ አባላት ጨምሮ ለሁሉም ልዩ ምስጋናችን እናቀርባለን።